Teninet/wrufail/addmesh the same person use this names. ስነ ፍጥርት /በጤንንት ሰጠኝ/

 ምስጢረ ሰማያትና ምስጢረ ኢትዮጵያ ፍልስፍና መጽሐፍ ስለ ስነ ፍጥረት ያቀረበውን ዘርዘር በማድረግ  አቀርባለሁ፡፡

ስነ ፍጥረት የፍጥረታት አመጣጥ የሚጀምረው ከግዝፍት፣ከጊዜና ከኃይል ነው፡፡የፍጥረታት ሁሉ የመጀመሪያ የሆኑት ግዝፈት፣ጊዜና ኃይል ናቸው፡፡ ስለ ፍጥረታት መናገር የተቻለውም እነዚህ በመኖራቸው ነው፡፡ ወይም ፍጥረታት ስለፍጥረታት/ራሳቸውን ጨምሮ/ ማወቅ፣ መገንዘብና ማስተዋል የጀመሩት ግዝፈት፣ ጊዜና ኃይል ከተፈጠሩ በኋላ ነው፡፡እነዚህን የመጀመሪያ ፍጥረታት የማይነጣጠሉ ቢሆኑም ለእኛ ስለየአንዳንዳቸው መጠነኛ መረዳት እንዲኖረን ያህል በተናጥል ልንመለከታቸው እንሞክር፡-

 ግዝፍት፡- 
 ግዝፈት ማለት የእንድ ነገር መኖር ወይም ህያውነትን የሚመለከት ነው፡፡ አንድ ነገር ግዝፈት አለው ስንል እራሱን ችሎ መታወቅ የሚችል ወይም ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ የራሱ የሆነ መለያ ወይም ባህሪ ያለው ወይም በራሱ መጠራት የሚችል ማለታችን ነው፡፡ ለምሳሌ፡-አየር ግዝፈት አለው፡፡ ድንጋይም ግዝፈት አለው፡፡ አየርንም ሆነ ድንጋይን ግዝፍት አላቸው ብልን የምንናገረው ያሉና ህያው የሆኑ ወይም የራሳቸው የሆነ ልዩ መለያ ያለቸው ወይም ድንጋይ ከዓየር የራሱ የሆነ ባህሪያት ስላሉት ነው እንጂ ስፍራ ስለሚይዝ ወይም ክብደት ስላለው አይደለም፡፡ በተመሳሳይ ህኔታ እንደ ምስጢረ ሰማያትና ምስጢረ ኢትጵያ አገላለጽ ነፍስ ግዝፈት ያለት ነች፡፡ ይህም ማለት ህያው የሆነች ወይም የራሷ የሆነ ልዩ ባህሪያት ያላት ስለሆነች ግዝፈት አላት እንላለን፡፡ ነገር ግን ነፍስ በምድራዊ ሰማያት /በፀሐይ ዙሪያ የሚገኑ አስራሁለት ስፍራዎችን የያዘ አካል/ እንደሚገኙ ፍጥረታት ቦታ የምትይዝና ክብደት ያላት አይደለችም፡፡ በጥቅሉ በምስጢረ ሰማያትና ምስጢረ ኢትዮጵያ ፍልስፍና መጽሐፍ አገላለጽ አንድ ነገር ግዝፍት አለው የምንለው ስፍራ ስለሚይዝና ክብደት ስላለው ወይም የታወቀ ያልታወቀ የተገኘ ያልተገኘ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ህያው የሆነና የራሱ ህልውና ያለው ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ 

ጊዜ፡-

ጊዜ እንደ ምስጢረ ሰማያትና ምስጢረ ኢትዮጵያ ፍልስፍና መጽሐፍ አገላለጽ ፍጥረታት ከተፈጠሩበት ጊዜ ጀምሮ አጠቃላይ የሆነውን ሂደት የሚመለከት ነው፡፡ ይህም ማለት በፍጥረታት ላይ የሚከናወነውን ማንኛውንም የለውጥ ሂደት የሚመለከት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-አንድ ድንጋይ ከተቀመጠበት ስፍራ ወደሌላ ስፍራ ቢዘዋወር መጀመሪያ ከተቀመጠበት ስፍራ ወደተዘዋወረበት ስፍራ ድረስ ያለው ሂደት ጊዜ ይሰኛል፡፡ በሌላ በኩል ይኸው ድንጋይ በተቀመጠበት ስፍራ ላይ ሆኖም ቢሆን በአጠቃላይ በሆነው የጊዜ ሂደት ለውጥ ውስጥ ያለ እንደመሆኑ በውስጡ የሚከናወነው የለውጥ ሂደትም ጊዜ ይሰኛል፡፡ እንደ ምስጢረ ሰማያት መጽሐፍ አገላለጽ ሁሉም ፍጥረት በለውጥ ሂደት ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም ፍጥረት በጊዜ ስር ይገኛል እንደማለት ነው፡፡

ኃይል፡-

በምስጢረ ሰማያትና ምስጢረ ኢትዮጵያ ፍልስፍና አገላለጽ  ኃይል ማለት አንድ ነገር በሌላው ነገር ላይ በጊዜ ሂደት ውስጥ ለውጥ ማምጣት የቻለበት አቅም ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ ሰው አንድ ድንጋይ ተሸክሞ ከሆነ ቦታ ወደ ሆነ ቦታ ቢያዘዋውረው ይህንን ድንጋይ በጊዜ ሂደት ውስጥ ከነበረበት ስፍራ ወደሊላ ስፍራ ማዘዋወር ወይም በድንጋዩ ላይ በጊዜ ሂደት ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ ያደረገበት አቅም ኃይል ይሰኛል፡፡ በሌላ በኩል ድናጋዩ ከስፍራው የተንቀሳቀሰው በራሱ ኃይል ሳይሆን ከሌላ ስፍራ በመጣ ኃይል ነው፡፡ ይህም ስለሆነ ኃይል ከራሱ ከፍጥረቱ ሊመነጭ አይችልም ወደሚል መደምደሚያ ላይ ያደርሰናል፡፡ ምነው ሰው በራሱ ኃይል ከሆነ ስፍራ ወደሌላ ስፍራ ይሄድ የለምን ቢባል ይህም ቢሆን ሰው ከስፍራ ስፍራ ሊዘዋር የሚችልበትን ኃይል ያመነጨው ከራሱ ሳይሆን ከሌላ / በተክሎች አማካኝነት ከፀሐይ/ በወሰደው ኃይል ነው፡፡ 

ይቀጥላል፡-