Agawu Awi Injibara Feres Gudisa blog err
- የአገው_አዊ ህዝብ መለያ የሆነውን የፈረስ ጉግስን ይመለከታል
የአገው የፈረስ ጉግስ ማህብር ፌስቲቫል እና ወቅታዊ አላስፈላጊ ለውጦች
- 1. የአገው የፈረስ ጉግስ ማህብር ስያሜን በተመለከተ
ይሄ ሰያሜ ህዝብ ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ስያሜ ሲሆን ስያሜወም ኢጣሊ ድል ከተደረገ በኅላ የአገው አረበኞች ያቋቋሙት የ79 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ የፈረሰኞች ማህበር ነው፡፡ ወደ አውማ የፈረስ ጉግስ ማህብር የመቀየር እንቅስቃሴ የተጀመርው በባለፈው አመት በUNESCO ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ ማድርግ በተጀመርበት ወቅት ነበር፡፡ ይሄ ስልት በማንነት ስም የተሰየመው የፈረስ ጉግስ ባህሉ የሆነው የአገው ህዝብ ሀለዎቱ እንዳይታወቅ የሚደርግ የድምሰሳ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ለነገሩ ይሄንን መቀየር ካልቻሉ አገው የሚባል አለ እንዴ የሚለውን ሀሳብ እንዴት ይጋፈጡታል መኖሩን ከሚያንፀባርቅባቸው ሁነቶች መካክል አንዱ ነውና፡፡ እናም የዛሬ ዓመት በተወሰነ መልኩ ያንፀባርቋትን የፌሰቲቫሉን ስያሜ ዛሬ ላይ ዋና አርዕስት አድርገው አመጧት፡፡ እና መጨረሻዋ ምን ለማድርግ ይመስላችኀል?ሀለዎት አገው እንዳይታይ ማድርግ ነው፡፡ ስለሆነም በአስችኳይ ሪክላሙ መቀየር አለበት #የአገው_የፈረስ_ጉግስ_ማህበር_ፌስቲቫል ተብሎ መስተካክል አለበት፡፡
- 2. በየሀገሩ እየተዘዋወር ሲከበር የነበረውን የማስቀረት አዝማሚያ
አሁንም ከዚህ ጋር በተያያዘ ማህበሩ ከተመሠረተ ጀምሮ የሁሉንም አባላቱን ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት ለማዳበርና ለማጠናከር ያስችል ዘንድ ተራ በተራ በየወረዳዎቹ በመዘዋወር በደስታና በፌሽታ የሚከበር ሁሉም የአገው ልጅ በጉጉት የሚጠብቀው የታላቅነት መገለጫ ፌስቲቫል ነው፡፡ ከዓመት በኀላ ያየነው ለውጥ አስገራሚ ነው ባለፈው ዓመት እንጅባራ ላይ ተከበር ዘንድሮም እንጅባራ ላይ እና ይሄ ምን ማለት ነው? we don't want unnecessary modification to our cultures.
ይሄ አካሄድ የጠቅላላ የማህበሩን አባላት የባለቤትነት ስሜት የሚያዳክምና እያሳደር ያለውን ማህበራዊና ፓለቲካዊ ተፅዕኖ የማሳደር ብቃቱን በመፈታተን ማህበሩን #ለመበተን_የተሠራ_አሻጥር መሆኑን መገመት የሚያዳግት አይሆንም፡፡
- 3. የሚዲያ ሽፍን
በባለፈው ዓመት ሚዲያዎች ፌስቲቫሉን የዘገቡት የአገው የፈርስ ጉግስ ፌስቲቫል በለው(ለዚህም ምስጋናየ ከፍ ያለ ነው) ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ አሁን ካለው የፓለቲካ ተፅዕኖና ከአያያዙ በመነሳት ምን ብለው ሊዘገቡ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ሊሆን የሚገባው 1. የፌስቲቫሉ ስያሜ ጥንት የነበርውና የቆየው #የአገው_የፈረስ_ጉግስ_ማህበር_ፌስቲቫል ተብሎ መስተካክል አለበት፡፡ 2. አከባብሩም በፌት እንደነበርው ተረኛ አዘጋጅ እየተመረጠ የሚያዘጋጅበት ሁኔታ መቀጠል አለበት፡፡ 3. አሁን በሥልጣን ላይ ያለው ገዥ ድርጅት አመራርና አባል የሆናችሁ ሁሉ እየተሠራ ያለውን ሸፍጥ መሞገትና ማስተካክያ ሊደርግ ይገባል 4. ይችን ሸፍጥ የሚተገብራት ስፓንሰር አድራጊ የተባለው ድርጅት ከሆነም ስፓንሰር ማድርጉን ሥርዓቱንና ወጉን በማያጠፍ መልኩ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስፓንሰር አድራጊው ባህላችንን ለመቀየጥና ለመለወጥ የመጣ ከሆነ.... 5. ሥነ ስርዓቱ የአገው የፈረስ ጉግስ የሚከወንበት እንጂ ሌላ የፓለቲካ ሥራ የሚሰራበት እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
ለባህሉ ለወጉ ለታሪኩ የቆመ ሁሉ ይህንን በአገው ህዝብ #መለያ_ምልክት በሆነው የፈረስ ጉግስ ባህል የመበተን የመቀየጥና የመለውጥ ሂደት ማስቆም ተገቢ ጉዳይ ነው፡፡
ደሞ የሚገርመው ይሄ ሁሉ ለውጥ በUNESCO ከመመዝገብ ጋር ምንም የሚያገናኘው የመሥፈርትም ይሁን ሌላ ምክንያት ሊሆን የሚችል ነገር የለም